ምግብ እና እርግዝና ለእርጉዝ እናቶች ጠቃሚ ሀሳብ

ADVERTISMENT

ምግብ እና እርግዝና
ለእርጉዝ እናቶች ጠቃሚ ሀሳብ

አሁንም ሆነ በወደፊት ህይወቱ ለልጅሽ ጤናማ አካላዊና አእምሮአዊ እድገት የተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊ ነው፡፡
ስለዚህ በእርግዝናሽ ወቅት ምግብሽ የሚከተሉትን ምግቦች እና ንጥረ ነገሮች ቢያካትት መልካም ነው፡፡

ኦሜጋ-3

በሳምንት አንዴ ወይም ሁለቴ በምግብሽ ውስጥ ዓሣ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በተለይ የዓሳ ዘይት ምንጭ የሆኑ ዓሦችን፡፡

ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች

በየቀኑ ቪታሚን ዲ (5 µg) ለመውሰድ ሞክሪ፡፡ በቪታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን ተመገቢ፡፡ ዓሣ፣ እንቁላል ወይም በቪታሚን ዲ ተጠናክሮ የተዘጋጀ ወተት ጠጪ፡፡ ለመጀመሪያዎቹ 12 የእርግዝና ሳምንታት ፎሊክ አሲድ (400 µg) በየቀኑ ብትወስጂ መልካም ነው፡፡

ካልሲየም

በቀን ሶስት ጊዜ ወተትና የወተት ውጤቶችን በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በየቀኑ ወተት፣ አይብና እርጎ ጥቂት-ጥቂት ሶስት ጊዜ ውሰጂ፡፡

ብረት (Iron)

በብረት ማዕድን የበለፀጉ ምግቦችን በቀን 2 ጊዜ በምግብሽ ውስጥ ለማካተት ሞክሪ፡፡ በብረት የበለፀጉ ምግቦች ውስጥ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል፣ ባቄላና አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች ይካተታሉ፡፡

ጣፋጮች

ጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦችና መጠጦች አልፎ-አልፎ በተለየ አጋጣሚ ብቻ ተመገቢ፡፡ ለምሳሌ በሳምንት ሁለቴ፡፡

አትክልትና ፍራፍሬ

በቀን ውስጥ ለ5 ጊዜ ያህል ከምግብሽ ጋር አትክልትና ፍራ-ፍራፍሬ ለመመገብ ሞክሪ፡፡